ዛሬ የአለምአቀፍ የአካባቢ ቀን ይከበራል፡፡
ቀኑን ስናስብ ለአካባቢ ጥበቃ ስራ ለረጅም ዘመናት ማሕበረሰባቸውን ያገለገሉ ጠንካራ ባለሙያዎችን አብረን እናስባለን፤ማሰብ ብቻም ሳይሆን ላበረከቱት አስተዋስኦም እናመሰግናለን፡፡እውቅናም እንሰጣለን!!ይህን ቀን ምክንያት በማድረግም ጠንካራና ታታሪ ባልደረባችንን እናስተዋውቃችሁ!!
አቶ ጌታቸው ወ/አረጋይ ይባላሉ፤በቀለም ኢትዮጵያ የፕሮጀክት ኦፊሰር ናቸው፡፡
ላለፉት ሁለት አመታት ቀለም ኢትዮጵያ ከ54,000 በላይ ከፍተኛ የገበያ ተፈላጊነት ያላቸው ችግኞችን እና 148 የውሃ ፓምፖችን ለአርሶ አደሮች በማከፋፈል ዘላቂ የሆነ የእርሻ ስራ እና የተራቆተ መሬቶችን መልሶ ማልማትን በማስተዋወቅ ረገድ አመርቂ ስራ ሰርተዋል።አቶ ጌታቸው ቀለም ኢትዮጵያ በሚሰራቸው የችግኝ ጣቢያ ማቋቋምና የችግኝ ስርጭት ስራዎች ሁሌም አሉ፤
አቶ ጌታቸው በግብርና ዘርፍ ለ34 ዓመታት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ያሉ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ተምሳሌት ናቸው።የችግኝ ማዕከላትን በማቋቋም፤ የችግኝ ስርጭት በማስተባበርና በማስፈፀም እንዲሁም በአርሶ አደሮች ቀየ በመገኘትና ሙያዊ እገዛ በመስጠት ያደረጉት አስተዋጽኦ ተጨባጭና ዘላቂ ለውጥ አምጥቷል።
ለሥነ-ምህዳር ተስማሚ ግብርናን በማስተዋወቅ፣ የማህበረሰብ ግንዛቤን በማነቃቃትና በማሳደግ ከፍ ያለ አስተዋሥኦ አድርገዋል፡፡ ከፀረ-ተባይ መከላከል እስከ ደን መልሶ ማልማት ድረስ ኃላፊነትና ጥንቃቄ የተሞላት የግብዓት አጠቃቀምን በማበረታታት ለአካባቢ ጥበቃ ጥብቅና መቆማቸውን ቀጥለዋል።
ድርጅታችንም አለምአቀፍ የአካባቢ ቀንን ምክንያት በማድረግ አቶ ጌታቸው ላከናወኗቸው ዘርፈ- ብዙ ስራዎቻቸው ልናመሰግናቸው እንወዳለን!
ነገን ከብክለት ለመጠበቅ ዛሬ እንስራ!!

ማስፈንጠሪያውን በመጫን ቪይዲዮን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@kelemethiopia/video/7512320020521815352