ወጣቶችን ማብቃት የወደፊት ህይወታቸውን ለመለወጥ ወሳኝ ነው!!
ወጣቶች የሀገር ታላቅ ሀብቶች ናቸው። ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ብዙ ወጣቶች በስራ አጥነት እና ለገበያ ተስማሚ የሆኑ ክህሎቶች ላይ በሚያጋጥማቸው ውስንነቶች ምክንያት ከፍተኛ ፈተናዎች ያጋጥሟቸዋል።ለዚህ ፈተና መፍትሄ የሚሆነው ወጣቶችን በተግባራዊ ክህሎቶችን ማስታጠቅ ነው፡፡ይህም ከሙያ ስልጠና ያለፈ ነገር አለው፤እሱም ከሙያ ክህሎት በተጨማሪ የተለያዩ የስራ ዕድሎችን መክፈት፣ ተስፋን ማደስ እና ጠንካራ ማህበረሰቦችን ለመገንባት ማገዝ ነው።
ዛሬ የዓለምአቀፍ ወጣቶች ክህሎት ቀን ነው፤ ቀኑ “Skills for a Shared Future ” በሚል መሪ ቃል ሲከበር፣ ወጣቶችን በተለያዩ የቴክኒክ እና የሙያ ክህሎቶችን የማብቃት አስፈላጊነትን በማጉላት የወደፊቱን ህይዎታቸውን የተሻለ ለማድረግ ያለመ እሳቤን ይዞ የሚከበር ነው።
እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ከሆነ፣ የቴክኒክና የሙያ ትምህርት ወጣቶችን ለሥራ ስምሪት፣ ለሥራ ፈጠራ፣ ለዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት እና ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚዎች ለመሸጋገር የሚያስፈልጋቸውን እውቀትና ብቃቶችን ያስታጥቃቸዋል።

ቀለም ኢትዮጵያ ይህንን ፍላጎት በመገንዘብ በስራ አጥነትና በተፈላጊ የስራ መስኮች መካከል ያለውን የክህሎት ክፍተት ለመሙላት በኮምቦልቻ ከተማ የስራ-ተኮር የወጣቶች የሙያ ክህሎት (Job-Oriented Youth Skills (JOYS)) ማሰልጠኛ ማዕከል አቋቁሞ ወጣቶችን በማሰልጠን ብቁ ባለሙያዎች እያፈራ ይገኛል።
ቀለም ኢትዮጵያ ይህንን ፍላጎት በመገንዘብ በስራ አጥነትና በተፈላጊ የስራ መስኮች መካከል ያለውን የክህሎት ክፍተት ለመሙላት በኮምቦልቻ ከተማ የስራ-ተኮር የወጣቶች የሙያ ክህሎት (Job-Oriented Youth Skills (JOYS)) ማሰልጠኛ ማዕከል አቋቁሞ ወጣቶችን በማሰልጠን ብቁ ባለሙያዎች እያፈራ ይገኛል::
በ JOYS የስልጠና ማዕከl አማካኝነት ከ1,000 በላይ ሥራ አጥ ወጣቶች በገበያ ከፍተኛ ተፈላጊነት ባላቸው አምስት የሙያ ዘርፎች ውስጥ የአጭር ጊዜ ሥልጠና አግኝተዋል። እነሱም፤
• የቧንቧ ሥራ
• የጂፕሰም ሥራ
• የሴራሚክ እና የወለል ንጣፍ ሥራ
• የልብስ ስፌት እና፣
• የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ሥራ ናቸው፡፡

እነዚህ የሙያ ዘርፎች በአሁኑ ወቅት ያለውን የሰው ኃይልና ከፍተኛ የሙያ ስራ ገበያ ፍላጎት መሰረት አድርገው በጥንቃቄ የተመረጡ ሲሆን፤ ይህም ሰልጣኞች በኢትዮጵያ እያደገ በመጣው የግንባታ እና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ውስጥ ሥራ እንዲያገኙ ወይም የራሳቸውን ስራ እንዲፈጥሩ አስችሏቸዋል።
ለብዙ ሰልጣኞች፣ ይህ ፕሮግራም የሙያ ህይወታቸውን እና ስለ ህይወት ያላቸውን አመለካከት የቀረጸ ወሳኝ የመሸጋገሪያ ምዕራፍ ሆኗል።
“ስልጠናው የፈጠራ ችሎታዬን አሳድጎልኛል፣ በራስ መተማመኔንም ገንብቶልኛል”
ወጣት እሸቱ የተፈጥሮ ተሰጥኦና ተግባራዊ የስራ ልምድ ነበረው። ይሁን እንጂ፣ መደበኛ ስልጠና ሳይወስድ፣ እድሎቹን ለማስፋት እና በሙያው ለመወዳደር ተቸግሮ ነበር። የወደፊት ህይወቱን ለማሻሻል ቆርጦ፣ በቀለም ኢትዮጵያ የ JOYS ስልጠና መርሃ ግብር ውስጥ ተመዘገበ። የክፍል ውስጥ ትምህርት እና የተግባራዊ ልምምድ ማድረጉ ችሎታውን አሻሻለለት።

“ስልጠናው ከጠበቅኩት በላይ ነበር” ሲል እሸቱ ያስታውሳል። “ቀደም ሲል የነበረኝን ባህላዊ ክህሎቶች አጠናክሮልኛል፣ ከአዳዲስ ቴክኒኮች ጋር አስተዋውቆኛል፣ እና የፈጠራ ችሎታዬን አሳድጎልኛል። ዛሬ፣ ተግባራዊ ልምድም ሆነ ሙያዊ እውቀት ስላለኝ በልበ ሙሉነት እሰራለሁ።” ሲል ይገልፃል እሸቱ፡፡
ዛሬ እሸቱ እያንዳንዱን ሥራ በከፍተኛ የራስ መተማመን፣ በሙያዊ ብቃት እና በፈጠራ ችሎታ ታግዞ ያከናውናል።ገቢውንም ማሳደግ ችሏል፡፡
ክህሎትን ወደ ገቢ መለወጥ
ኤርምያስ ሌላኛው ሰልጣኛችን ሲሆን፣ ስልጠናው የራሱን ስራ ሰርቶ የገንዘብ ነጻነት እንዲያገኝ አስችሎታል። የጂፕሰም ስራ ስልጠናውን ካጠናቀቀ በኋላ፣ እናቱን ለመደገፍና የወደፊት ህይዎቱን ለማቀድ የሚያስችለውን የተረጋጋ ገቢ በፍጥነት እንዲያገኝ አስችሎታል።
“ይህ የአጭር ጊዜ ስልጠና ህይወቴን ሙሉ በሙሉ ለውጦታል” ይላል ኤርምያስ። “የምሰራውን ስራ እወደዋለሁ፣ እናም በጋለ ስሜት እሰራለሁ። ጥራት ያለው ስራ በማቅረብ እና የደንበኞቼን እምነት በማግኘት፣ ተጨማሪ ፕሮጀክቶችን ለመስራት እፈልጋለሁ። አሁን የተሻለ የወደፊት ሕይወት ለመገንባት ገንዘብ እያጠራቀምኩ ነው።” ብሏል ኤርሚያስ
የወደፊት ራዕዩ ከራሱ ስኬት በላይ ይዘልቃል። ኤርሚያስ ስራውን ለማስፋት፣ ተጨማሪ አዲስ ሠራተኞችን ለመቅጠር እና ለሌሎች ሥራ አጥ ወጣቶች የስራ እድሎችን ለመፍጠር ህልም አለው።
“ዓላማዬ አዳዲስ ሰልጣኞችን መቅጠር፣ ትላልቅ የስራ ፕሮጀክቶችን መስራት እና ለሌሎች የስራ እድሎችን መፍጠር ነው።” ይላል ኤርሚያስ
እንቅፋቶችን መስበር፣ ህልሞችን መገንባት
ለሃናን ኢብራሂም የጆይስ ማዕከል የተዛባ አመለካከቶችን ለመጋፈጥና አዳዲስ እድሎችን ለመዳሠስ እድል ፈጥሮላታል፡፡ በተለምዶ የወንዶች ሥራ ተደርጎ በሚታይ ሙያ ውስጥ፣ ሃናን በጂፕሰም እና በሴራሚክ ሥራ ላይ ልዩ ሙያ ለመማር ወሰነች። በጽናት ስልጠናዋን ካጠናቀቀች በኋላ ስኬትን የሚወስነው ጾታ ሳይሆን ክህሎት እና ቁርጠኝነት መሆኑን አረጋገጠች።

“ለቀለም ኢትዮጵያ ምስጋና ይግባውና፣ ባለሙያ ሆኛለሁ” ስትል ሃናን በኩራት ትናገራለች።
ዛሬ በቴክኒክ ዘርፎች የሙያ ሥራ ለመጀመር ለሚመኙ ሌሎች ወጣት ሴቶች አነቃቂ ምሳሌ ሆናለች። የእርሷ ምኞት ከግል ስኬትም ያለፈ ነው። ሌሎች ሴቶች ልዩ ሙያ የሚጠይቁ ሥራዎች ላይ እንዲሰማሩ ለማበረታታት እና ለማህበረሰቧ ዘላቂ አስተዋጽኦ ለማበርከት ትሻለች።
ተከታታይ ተጽዕኖ የመፍጠር ጉዞ
የጆይስ ማዕከል ተጽእኖ ከግለሰብ ተመራቂዎች አልፎ ማህበረሰባዊ ተፅእኖው አሻራውን እያሳየ ነው፡፡ብዙዎቹ
• የተረጋጋ የሥራ ዕድል መፍጠር ችለዋል
• የራሳቸውን ስራ መጀመር ችለዋል
• ለሌሎች ሥራ አጥ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ችለዋል።
“ለቀለም ኢትዮጵያ ምስጋና ይግባውና፣ ባለሙያ ሆኛለሁ” ስትል ሃናን በኩራት ትናገራለች።
ዛሬ በቴክኒክ ዘርፎች የሙያ ሥራ ለመጀመር ለሚመኙ ሌሎች ወጣት ሴቶች አነቃቂ ምሳሌ ሆናለች። የእርሷ ምኞት ከግል ስኬትም ያለፈ ነው። ሌሎች ሴቶች ልዩ ሙያ የሚጠይቁ ሥራዎች ላይ እንዲሰማሩ ለማበረታታት እና ለማህበረሰቧ ዘላቂ አስተዋጽኦ ለማበርከት ትሻለች።
ተከታታይ ተጽዕኖ የመፍጠር ጉዞ
የጆይስ ማዕከል ተጽእኖ ከግለሰብ ተመራቂዎች አልፎ ማህበረሰባዊ ተፅእኖው አሻራውን እያሳየ ነው፡፡ብዙዎቹ
• የተረጋጋ የሥራ ዕድል መፍጠር ችለዋል
• የራሳቸውን ስራ መጀመር ችለዋል
• ለሌሎች ሥራ አጥ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ችለዋል።
• ቤተሰቦቻቸውን መደገፍ እና ለአካባቢያቸው ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ ማድረግም ችለዋል።
ወጣቶቹ የሚያገኟቸው ክህሎቶች በማንም ሊነጠቁ የማይችሉ የዕድሜ ልክ ሀብቶች ሆነዋል። ተመራቂዎች ስኬታማ ሲሆኑ፣ እውቀታቸውን በማካፈል፣ የስራ ዕድሎችን በመፍጠር እና ሌሎችም ውጤታማ የኑሮ ጎዳናን እንዲከተሉ በማነሳሳት የፕሮግራሙን ተጽዕኖና አድማስ ያሰፋሉ።
በወጣቶች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ማለት ለወደፊቱ ትውልድ ኢንቨስት ማድረግ ማለት ነው።
ለወጣቶች ተግባራዊ ክህሎቶችን ማጎናጸፍ ማለት አንድን ሙያ ከማስተማር ያለፈ ትርጉም አለው።በራስ መተማመንን ይገነባል፤ክብርንም ያጎናፅፋል፡፡ይህ ሥራ ፈጣሪዎችን ማፍራት ብቻ ሳይሆን የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊ እድገትም ያነቃቃል። ከሁሉም በላይ ደግሞ፣ ወጣቶች በራሳቸው ማህበረሰብ ውስጥ የለውጥ አራማጆች እንዲሆኑ ብቁ ያደርጋቸዋል::
የዓለም የወጣቶች ክህሎት ቀንን “Skills for a Shared Future” በሚል መሪ ቃል ስናከብር፣ ከቀለም ኢትዮጵያ ጆይስ ማዕከል የተገኙ የስኬት ታሪኮች በወጣቶች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ማንኛውም ማህበረሰብ ሊያደርጋቸው ከሚችላቸው እጅግ ጠቃሚ ኢንቨስትመንቶች አንዱ መሆኑን ያስታውሰናል።


