+251-113-72-68-76

Login

Sign Up

After creating an account, you'll be able to track your payment status, track the confirmation.
Username*
Password*
Confirm Password*
First Name*
Last Name*
Email*
Phone*
Contact Address
Country*
* Creating an account means you're okay with our Terms of Service and Privacy Statement.
Please agree to all the terms and conditions before proceeding to the next step

Already a member?

Login

“የፕላስቲክ ብክለትን እናሸንፍ”

ዓለምአቀፍ የአካባቢ ቀን

ነገ የአለምአቀፍ የአካባቢ ቀን ይከበራል፣ ይህን ቀን ምክንያት በማድረግ እየጨመረ ስላለው የአካባ ብክለት ስጋትና አደጋ እንዲሁም ድርጅታችን አካባቢን ለመጠበቅ ያደረገውን ጥረት እናስታውስዎታለን።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የአየር ለውጥ፤የጎርፍ፣ የድርቅ እና የሰደድ እሳት ጉዳት ሳይንሳዊ ስጋት ብቻ ሳይሆን ቤታችንን፣ መሠረተ ልማታችንን፣ ኑሮአችንን እና የምግብ ስርዓታችንን በቀጥታ እየጎዳ ያለ ፈተና ነው።

መሰል የአየር ለውጦች ከአካባቢ ብክለት ጋር በቀጥታ ይገናኛሉ፤አካባቢን ከሚበክሉ ነገሮች መካከል ደግሞ የፕላስቲክ ቆሻሻዎች ከፍተኛ የጤናና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ፡፡አካባቢን ከብክለት መጠበቅ ያለውን ጥቅም ለማስተማር ማህበረሰቡን ማነቃቃት እና ለበጎ እንቅስቃሴ ማነሳሳት ተገቢ አካሄድ በመሆኑም የዘንድሮው የአለም የአካባቢ ቀን “የፕላስቲክ ብክለት እናሸንፍ” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ኩነቶች እየታሰበ ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያ በግብርና ላይ ባላት ጥገኝነት ምክንያት የአየር ሁኔታ ለውጦች ለከፋ አደጋ ያጋልጣታል፤በመሆኑም የሰብል ምርት እንዲቀንስ፣ የእንስሳት ሞት እና የአካባቢ መራቆት እንዲከሰት ምክንያት ይሆናል። ይህም በገጠር የሚኖሩ ማህበረሰቦችን የምግብ ዋስትና እና የማህበረ-ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት የሚፈትን ሆኗል።

እ.እ.አ. በ 2025 በአለምአቀፍ ደረጃ ከ 516 ሚሊዮን ቶን በላይ ፕላስቲክ ጥቅም ላይ ይውላል ተብሎ ይገመታል፡፡በአገራችንም የፕላስቲክ ምርቶችን መጠቀም የተለመደ መሆኑ እንዳለ ሆኖ የፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ላይ ግን በርካታ ችግሮች ይታያሉ፡፡የፕላስቲክ ቆሻሻዎች በአግባቡ ባለመሰብሰባቸው ምክንያት የውሃ መፋሰሻዎች ሲደፈኑ፤የጎርፍ ውሃም በአግባቡ እንዳይፈስ ሲያግዱ እናያለን፡፡

ከዚህ ተጨማሪም መሰል ብክለቶች በወንዞች እና በእርሻ መሬቶች ላይ የውሃ ምንጮችን የሚበክሉ፤የአፈርን ጥራት የሚቀንሱ፤ የጤና እና የአካባቢ አደጋዎችን የሚያስከትሉ እና የዱር እንስሳትን አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸው፡፡

ይህንን ችግር ለመፍታት ቀለም ኢትዮጵያ የአካባቢን ንጽህና ለመጠበቅ የሚያግዙ ጠቃሚ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡የፕላስቲክ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል እና የማህበረሰቡ የግንዛቤ ለማሳደግ ቀለም ኢትዮጵያ በ UYEEP ፕሮጀክቱ በኩል ሰፊ ጅምር ስራዎችን በመስራት ላይ ነው።

የዚህ ፕሮጀክት አላማ ስራ አጥ ወጣቶችን በማሰልጠን የፕላስቲክ ቆሻሻዎችን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ገቢ እንዲያኙ ለማገዝ ያለመ ነው። ይህ ስራ በአማራ ክልል በሚገኙ ስድስት ከተሞች ማለትም በደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ወልድያ፣ ባቲ፣ ከሚሴ እና ሀይቅ የሚካሄድ ሲሆን፤ ከ350 በላይ ወጣቶች የፕላስቲክ ቆሻሻ በመሰብሰብ መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችላቸው ስልጠናና የመሳሪያ ድጋፍ አግኝተዋል።ድጋፎቹም 6 የፕላስቲክ መጨፍለቂያ ማሽን፤የተሰበሰቡ የፕላስቲክ ቆሻሻዎችን ለማጓጓዝ የሚረዳ 6 ባለሶስት እግር ባጃጅ፣ለስድስቱም ከተሞች 100 የቆሻሻ ማጠራቀሚያ እንዲሁም የተለያዩ የደህንነት መጠበቂያ አልባሳት እገዛ ተደርጎላቸዋል፡፡

የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ ከተለያዩ የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤት ለተውጣጡ 60 በጎ ፈቃደኛ የማህበረሰብ ውይይት አመቻቾች የአካባቢ ጥበቃ፤ቆሻሻ አወጋገድና አያያዝን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ተሰጥቷል፡፡በጎ ፈቃደኞቹም ለ 6 ሺህ የማህበረሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት ላይ ናቸው፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራው ለበርካታ ሰዎች እንዲደርስ በሬዲዮ ፎረም ድራማ የታገዘ ውይይት በማድረግ፤የቀጥታ ህዝብ አሳታፊ ውይይትና የባለሙያ ትምህርት በመስጠት 200 ሺህ የሚሆኑ አድማጮችን ለመድረስ እየሰራን እንገኛለን፡፡

ከዚህ ፕሮጀክት በተጨማሪ በችግኝ ማፍያና ማከፋፈያ ጣቢያችን ባለፉት ሁለት አመታት ብቻ ወደ 54 ሺህ የሚጠጉ ገበያ መር ችግኞችን በማከፋፈል የአካባቢ ጥበቃ ስራውን ከማገዛችን በተጨማሪ የአርሶአደሮችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጠናከር እየሰራን እንገኛለን፡፡

ቀለም ኢትዮጵያ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል በሚሳተፍባቸው ፕሮጀክቶች ሁሉ የአካባቢ ጥበቃ ላይ መስራት ከብክለት የፀዳ አካባቢን ለመጪው ትውልድ ለማስተለለፍ እንደሚያግዝ ያምናል፤በዚህ ስራው የዜጎችን ህይዎት ለማሻሻል አሁንም ጥረቱን ይቀጥላል፡፡

የፕላስቲክ ብክለት ደረጃው እየጨመረ በመምጣቱ ዘርፈ-ብዙ ስራዎች ያስፈልጋሉ፤የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችም በስፋት ሊሰሩ እንደሚገባ እናምናለን፡፡

በጋራ አንድ ላይ ከብክለት ነፃ የሆነች ጠንካራ ኢትዮጵያን መፍጠር እንችላለን!!

ነገን ከብክለት ለመጠበቅ ዛሬ እንስራ!!!

Related Posts

Leave a Reply